Welcome to Lideta Subcity Woreda 8 Public Service and HR Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ራዕይአችን በ2022 ዓ.ም ተልዕኮውን በብቃት መፈጸምና ማስፈጸም የሚችል እና በስነ-ምግባሩ የተመሰገነ ነፃና ገለልተኛ ፐብሊክ ሰርቪስ ተፈጥሮ ማየትት ነዉ፡፡

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የክ/ከተማችን ብሎም የወረዳችን ነዋሪ ፈጣን፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው አገልግሎት የማግኘት መብት ያለው በመሆኑ ይህንን የህዝባችንን ፋላጎት ዕውን ከማድረግ አኳያ የአገልገሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ ራሱን እያሻሻለ እና እያሰደገ የሚሄድ በስነምግባሩ የተመሰገነ፣ ነፃ ገለልተኛ የሆነ ፐብሊክ ሰርቪስ መፍጠር ዋነኛው ጉዳይ ሊሆን ይገባል፡፡

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለዉጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በስነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰዉ ኃይል እንዲመራ የማድረግ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የህዝቡን የመገልገል መብቶች በተሟላ ሁኔታ በማስጠበቅ የዜጎች.... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ አምባቸው ተፈራ , የልደታ ወረዳ 8 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

ዋና ዋና አገልግሎቶች

የሰው ሀብት ክትትልና ድጋፍ አገልግሎት
የሰው ሀብት ስምሪት እና መረጃ አግልግሎት
የሰው ሀብት ኦዲት አገልግሎት / HR Audit Services
የሰው ሀብት ቅሬታና አቤቱታ አገልግሎት
የሰው ሀብት ልማትና ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት
የወረዳ ማሰፈጸም አቅም ግንባታ አገልግሎት
የአገልግልት ስታንዳርዳይዜሽንና ምዘና አገልግሎት
የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ አገልግሎት

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች

በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡