ዜና | Oduu | News
የእንኳን ደስ አላችሁ የምስራችና የክብር መግለጫ! ታሪክ ዳግም ተጽፏል፤ ስኬት በድጋሚ ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጎርፏል!!!

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለተከታታይ ጊዜያት ያስመዘገበውን የላቀ እና አርአያነት ያለው አፈጻጸም በመቀጠል፣ በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ደረጃን በመያዝ በከተማችን አዲስ አበባ ደምቆ ወጥቷል። በዚህም ታላቅ ስኬት ለ2ኛ ጊዜ ተከታታይ የመኪና ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል! ይህ ስኬት ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን የዕለት ተዕለት የትጋት፣ የቁርጠኝነት እና የህብረት ውጤት ነው። ለአንጸባራቂው ስኬት ባለቤቶች የላቀ ምስጋና ይህ ታሪካዊ ድል እንዲመዘገብ ሌሊትና ቀን ሳይታክቱ ለደከሙት፦ ለተከበሩ የወረዳው ነዋሪዎች፡ ለልማትና ለለውጥ ሁልጊዜም ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ንቁ ተሳትፎ፣ ለላቀው አመራርና ቁርጠኛ ሰራተኞች፡ ህዝብን በታማኝነት፣ በቅልጥፍና እና በከፍተኛ ተነሳሽነት በማገልገል ለምታሳዩት ድንቅ የስራ ባህል፣ ለባለድርሻ አካላት፡ በየደረጃው ከጎናችን በመቆም ለምታደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ፣ ልባዊ እና የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን! ይህ ድል የእናንተ የጋራ የድካም ፍሬ ነው! በከተማችን ከንቲባ የተበረከተ የክብር ምስጋና ሽልማት አመራሩና ሰራተኛው ይበልጥ እንዲነቃቃ፣ የውድድር መንፈስ እንዲሰፍን እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲሻሻል የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች ይህንን የመሰለ ታላቅ ማበረታቻ ሽልማት ለሚያበረክቱት ለተከበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ስራዎቻቸውን በማድነቅ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ይህ እውቅና ነገ ከዛሬ ይበልጥ ጠንክረን እንድንሰራ ትልቅ ጉልበት ይሆነናል። የወደፊት ራእያችን ወረዳ 8 ሁልጊዜም የስኬት እና የልማት ተምሳሌት ሆኖ ይቀጥላል። ይህ የ2ኛ ጊዜ የመኪና ሽልማት የመጨረሻችን ሳይሆን፣ ወደ ላቀ የህዝብ አገልግሎት እና የከተማችንን ብልጽግና ወደ ማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን የነዳጅ ያህል ነው። የጋራ ስራ፣ የጋራ ስኬት! እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! አቶ ደረጄ ፈይሳ የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ሥራ አስፈፃሚ

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 አስተዳደር "ኑ ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የመንግስት ሰራተኞች በጊዶ ዋሻ ችግኝ ተክለዋል።

በእለቱም ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ ከክረምት በጎ ፍቃድ አንዱ የሆነዉ የችግኝ ተከላ ነዉ ችግኝ በመትከል ሁሉም አካላት አሻራ በማስቀመጥ የአረንጓዴን ልምላሜን በማሳደግ የሀገራችንን የአየር ንብረት ተስማሚ ማድረግ አለብን ብሏል። የወረዳ 08 ብልግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢንጅነር ይትባረክ ብርሃነ በበኩላቸው ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም አለብን የምንተክላቸዉን ችግኞች በጥንቃቄ በመትከል አሻራችንን ማሳረፍ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ለመንግስት ሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠሪያ የጣት አሻራ አፈፃፀም ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ተሰጠ!

የልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠሪያ የጣት አሻራ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል። የወረዳ 08 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምባቸው ተፈራ የጣት አሻራ ያስፈለገበት ምክንያት በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም ሰራተኞች በጣት አሻራ የሰዓት መቆጣጠሪያ ላይ ደረጃውን የጠበቀ፣ አስተማማኝ ፣ቀልጣፋ፣ተጠያቂነት እና ግልፅነት እንዲኖረው ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል ። አቶ አምባቸዉ አክለዉም የጣት አሻራ ከሀምሌ 01/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተናግረዉ የመንግስት ሰራተኞች በዓመት ፍቃድ በወሊድ ፍቃድ በህመም እና በሌሎች በመስራያ ቤቱ በሚታወቁ ህጋዊ ፍቃዶች በስራ በማይገኙበት ጊዜ ለሰው ሃብት አስተዳደሩ ክፍል በሲስተሙ የቀረበበትን ምክንያት ማረጋገጥ አለበት ፤ሆኖም የታየዘው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ወደ መደበኛ የአሻራ ቁጥጥር ስርዓት እንዲገባ ተናግረዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የፋይናስ ጽ/ቤት የአይሲቲ ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ታደሰ ሁሉም የወረዳው ቋሚ ሰራተኞች ለአሻራ መስጠት እንዳለባቸው በመግለፅ ሁሉም ሰራተኛ የአተገባበር መመሪያው ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስበዋል:: በዉይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 የባለጉዳይ ቀን መሰረት በማድረግ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጡ ከምንግዚውም የተሻለ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተገልጋዮች ተናገሩ ።

ተገልጋዮች እንደገለፁት ባለሙያዎች እና አመራሮች የባለጉዳይን ቀን ያለምንም እንግልት ለማገልገል በስራ ገበታቸዉ ላይ በመሆን ቀልጣፍ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በተደረገዉ ምልከታ ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠትና ተገልጋዩን ከእንግልት የፀዳ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ የማሳደግ የትኩረት አቅጣጫ መሆን እንዳለበት ያነጋገርናቸው ባለጉዳዮች ገልፀዋል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤን መቋቋሙ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ላቀ ያለ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሃብት አስተዳደር ጽ/ቤት በ6 ወር በመማክርት ጉባኤው የተከናወኑ ተግባራት ተገምግሟል። በመድረኩ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የተውጣጡ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎችና የመማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚዎች የተሳተፉ ሲሆን የክ/ከተማው ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ ሙሉጌታ ንጋቱ መማክርት ጉባኤ ያከናወናቸውን ተግባራት ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ እንዳሉት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መማክርት ጉባኤው ተገልጋዩንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት ያሉ አቅሞችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋ በርካታ ተግባራት መሰራታቸውን ገልጸዋል ። ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ መማክርት ጉባኤው ያለው ሚና የጎላ ያሉት ወ/ሮ መቅደስ አያይው አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ መማክርት ጉባኤው ያለው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የመድረኩ ከተሳታፊዎችም መማክርት ጉባኤ መቋቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን ላይ የተሻለ ለውጥ እያመጣ እንደሆነ አንስተዋል።

image
image
image
image